Wednesday, 23 November 2016
ጸሀይ በቁርአን እይታ
ሙስሊሞች ወንድሞቻችንን ስለቁርአን ስትጠይቋቸው የሚገርም መልስ ይሰጧችኋል፡፡ ቁርአን ሳይንስ ያረጋገጠው፣ ታሪክ የመሰከረለት የአጻጻፍ ምጥቀቱ ፍጹም ወደር የማይገኝለት እንደሆነ ይነግሯችኋል፡፡ቁርአን በሰማይ ሰሌዳ የተጻፈና ከዛ ተገልብጦ ወደ ምድር የወረደ አስደናቂ መጽሀፍ እንደሆነ ሳይታክቱ ይነግሯችኋል፡፡ ከዛ ማንበብ እንዳለባችሁ ትወስኑና ሰታነቡ በተቃራኒው ሳይንስ ያላረጋገጣቸው፣ ታሪክ የማያውቃቸው፣ ተረት መሰል ጽሁፎች የተጠራቀሙበት መጽሐፍ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡እስኪ አንድ የቁርዓን ታሪክ ላካፍላችሁና በዚህ የቁርዓን ታሪክ አስመልክቶ የሚገርም ትንታኔ የሰጠንን የሙስሊም ምሁር እንመልከት፡፡
ታሪኩ የሚገኘው በቁርዓን 18፡83-86 ነው እንዲህ ይነባባል፡፡
“ከዙልቀርነይንም ይጠይቁሃል በእናንተ ላይ ከእርሱ አነባለሁ፡፡ በላቸው እና እኛ ለርሱ በምድር አስመቸነው፡፡ ከነገሩ ሁሉ (መዳረሻ) መንገድን ሰጠነው፡፡ መንገድንመ (ወደ ምዕራብ) ተከተለ፡፡ ወደ ጸሀይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት፡፡ በአጠገቧም ህዝቦችን አገኘ፡፡……….”
ሒሊል ካሀን፣ ዩሱፍ አሊ፣ሻኪር፣ ፒክቶል እና አርቤሪ ቁርአንን ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎሙ ሰዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ከላይ የተገለጸውን የቁርአን አንቀጽ የተረጎሙት በተመሳሳይ መልኩ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እንደአብዘኞቹ ሙስሊሞች እምነት ዙልቀርነይን ታላቁ እስክንድር እንደሆነ ይገመታል፡፡ አንግዲህ ዙልቀርነይን ወደ ምዕራብ ሲጓዝ ጸሀይ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ስትገባ እንዳያት ነው ይህ የቁርአን አንቀጽ የሚገልጽልን፡፡ አስቡት ከመሬት ጋር ስትነጻጸር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ በግዝፈት (በትልቅነት) የምትልቀው ጸሀይ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ስትገባ፣ ከመሬት ያላት ርቀት 149 ሚሊዮን እንደሆነ የምትገመተው ጸሀይ ጋር ለመድረስ ዙልቃርነይን ሰዓታት ብቻ ሲፈጅበት፡፡ ለመሆኑ ዙልቀርነይን በምን ትራንስፖርት ሄዶ ነው በሰአታተት እድሜ ጸሀይ ጋር መድረስ የቻለው፡፡ ሌላው አስቂኝ ነገር ደግሞ አጠገቧ ህዝቦች መኖራቸው ነው፡፡የጸሀይ ውጫዊ አካል በአማካይ 6000 ዲግሪ ሲንቲግሬድ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በዚህ የሙቀት መጠን ህዝቦች ሲኖሩ አስቡት፡፡ የነዚህ ህዝቦች ስጋ ከምን አይነት ነገር ቢሰራ ነው ይህን ያክል የሙቀት መጠን መቋቋም የሚችለው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ሳይንስ ያረጋገጠው መጽሀፍ ማለት፡፡
ሌላው ይህንን ተረት መሰል ታሪክ ትንታኔ መሰጠት የፈለገ አንድ ምሁር አለ፡፡ ዶ/ር ዛኪር ናይክ ይባላል፡፡ ዶ/ር ዛኪር በዚህ የቁርዓን አንቀጽ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት ዙልቀርነይን በእውነት ጸሀይን በአካል ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ እንደገባች አላየትም ነገር ግን የምዕራብን አቅጣጫ ተከትሎ ሲሄድ ጸሀይ ጠለቀችበት እዛም ህዝቦችን አገኘ፡፡ ጥቁር ጭቃ አየሁ ያለው አላህ ሊያሳየው የፈለገው ነገር ስላለ እንጂ በእውን እንደዛ አይነት ነገር አላየም በማለት የእሱን ትምህርት ለሚከታተሉ ሰዎች እፎይታ ለመስጠት ሞክሯል፡፡ ይህ አስተያየት አይን እያዩ ከመዝረፍ የሚተናነስ ትንታኔ አይደለም፡፡
የሚያሳዝነው ይህንን የዛኪር ትንታኔ ራሱ የእስላሞች ነብይ ውድቅ ሲደርገው እናያለን፡፡ በሙስሊሞች ታማኝ ከሚባሉ የሀዲስ ዘገባዎች አንዱ አቡ ዳውድ ነው፡፡ ሱናን አቡ ዳውድ ሃዲስ ቁጥር 3991 “አቡዛር (የመሀመድ ጓደኛ) እንደተናገረው ‘አንድ ጊዜ እኔና አላህ መልዕክተኛ አህያ ጀርባ አብረን ተቀምጠን እየሄድን ነበር፡፡ እኔ የተቀመጥኩት ከኋላ ነበር፡፡ ጸሀይ እየጠለቀች ነበር፡፡ ወዲያው የአላህ ነብይ ጸሃይዋ የት እንደምትጠልቅ ታውቃለህ ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም አላህና ነብዩ ያውቃሉ ብየ መለስኩ፡፡ ነብዩም ጸሀይ የምትጠልቀው ሙቅ በሆነ ምንጭ ውሃ ነው ሲል መለሰልኝ ሲል ዘግቦታል፡፡ ምንአልባት ዶ/ር ዛኪር ለዚህ የሀዲስ ታሪክ ትንታኔ ለመስጠት ምን አይነት ቀዳዳ ይጠቀም ይሆን፡፡ በዚህ ሙስሊሞች በሚያምኑበት የሀዲስ ጽሁፍ ዙልቀርነይነም ሆነ ዛኪር ሳይሆን መሀመድ የጸሀይ መጥለቂያ ሙቅ በሆነች የምንጭ ውሃ መሆኑን እንደተናገረ ተዘግቧል፡፡
ስለዚህ እዚህ ላይ ሁለት አጨቃጫቂ ነገሮች እናያለን መሀመድና ጸሀይ የምትጠልቀው ሙቅ የምንጭ ውሃ ነው ሲለን፣ አላህ ደግሞ በበኩሉ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ እንደምትገባ ነግሮናል፡፡ በዛ ላይ ምሁሩ ዛኪር ደግሞ ጸሀይ ምንም ነገር ላይ እንደማትጠለቅ በመናገር አላህንና መሀመድን ለማስተካከል ሞክሯል፡፡ በመሆኑም ዛኪር መሀመድና አላህን ተሳድቧል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞች ይህንን ዛኪርን አንድ ልትሉት ይገባል፡፡ ምክንያቱም የፈጣሪያችሁንና የነብያችሁን ቃል ሊያስተካክል ስለሞከረ ይብቃህ ሊባል ይገባዋል፡፡ አይመስላችሁም፡፡
በመጨረሻም በዚህ ላይ ሶስት አማራጭ ልስጣችሁና ውሳኔውን ለእናንተ እተወዋለሁ፡፡
1ኛ.ጥሩ ሙስሊም ከሆናችሁ በዚሁ ተረት ተረት በሚሸት መጽሃፋችሁ አምናችሁ መቀጠል
2ኛ. መጥፎ ሙስሊም ከሆናችሁ እንደዛኪር ትንታኔ እየሰጣችሁ አላህንና መሀመድን መሳደብ
3ኛ. እስልምናን መተውና ወደ እውነቱ መመለስ፡፡ እውነቱ ደግሞ እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ወደ እሱ በመምጣት ሰላማችሁንና የዘላለም ህይወትን ትወርሳላችሁ፡፡ እግዚአብሄር ይርዳችሁ፡፡ እኔ እናተን ብሆን ግን የምመርጠው 3ኛውን አማራጭ ነበር፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment