ሙስሊሞች አላህ ለአብርሃም፣ ለሙሴ፣ ለዳዊትና ለክርስቶስ መጽሐፍ እንዳወረደ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ለአብርህም የወረደው መጽሐፍ የጠፋ ሲሆን፣ ለዳዊት የተሰጠው መጽሐፍ (ዘቡር)፣ ለሙሴ የተሰጠው መጽሐፍ (ተውራት) ፣ ለክርስቶስ የተሰጠው መጽሐፍ (ኢንጅል) የተቀየሩና የተበረዙ መጽሃፍት እንደሆኑ ሲናገሩ ይሰማል፡፡
በመጨረሻ ለሙሀመድ የወረደው መጽሀፍ (ቁርዓን) ብቻ ሳይበረዝ የቆየና ነጥብ አንኳን ያልተቀየረ አንደሆነ በተለያዩ ጽሁፎችና የሚዲያ አውታሮች ለተከታዮቻቸው ሲናገሩ እናስተውላል፡፡ ይህ ተዓምራዊ መጽሐፍ (ሙስሊሞች አንደሚሉት) በሙሀመድ ጊዜ ከነበረው ጋር ፍጹም ተመሳሳይ መሆኑን ሲነገሩን እንሰማለን፡፡የቁርዓን ተዓምር በዚህ ብቻ እንደማይወሰን ነው ሙስሊሞች ሊያስረዱን የሚሞክሩት የስነ-ጽሁፍ ምጥቀቱ በአለም ካሉ የስነ-ጽሁፍ ስብስቦች የላቀና ምንም የማይወዳደር አስደናቂ መጽሀፍ እንደሆነም ነው የሚያስረዱን፡፡ የዚህ የስነጽሁፍ ምጥቀት ዋና ምክንያት ደግሞ የአምላክ ቃል በመሆኑ ነው በማለት ይገልጹልናል፡፡ አውነቱ ግን ይህ አይደለም፡፡ ቁርዓን የጽሁፍ ስህተቶች ያሉበት መጽሀፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ የስዋሰው ስህተቶች (Grammatical Errors) ያሉበት እንደሆነ ነው ያየነው፡፡ እስኪ እነዚህ የቁርዓን የስዋሰው ስህተቶች (Grammatical Errors) አንድ በአንድ እንመልከት፡፡
ሰህተት 1
በሱራ 5፡69 "Innal-laziina 'aamanuu wal-laziina haaduu was-Saabi'uuna wan-Nasaaraa man 'aamana bilaahi wal-Yawmil-'Aakhiri wa 'amila saali-hanfalaa khaw-fun 'alay-him wa laa hum yah-zanuun." ከላይ ባየነው የቁርዓን አያ (verse) Saabi'uuna የሚለው ቃል በስሀተት የገባና የሰዋሰው ስህተት ያለበት ነው፡፡ ነገር ግን መግባት የነበረበት Saabi'iina የሚለው ቃል ነበር፡፡ ይህ ቃል ቀጣይ በምናያቸው ሁለት የቁርዓን ምዕራፎች ባሉ አያዎች በትክክለኛ የሰዋሰው አገባብ የተጻፈ እንደሆነ እናያለን፡፡ በሱራ 2፡62 "Innal-laziina 'aamanuu wal-laziina haaduu wan-Nasaaraa was-Saabi'iina ..." በሱራ 22፡17 "Innal-laziina 'aamanuu wal-laziina haaduu was-Saabi'iina wan-Nasaaraa ..." ስለዚህ በሱራ 5፡69 'uuna የሚለው ቃል አንደአመልካች ወይም ጠቋሚ ወይም የሚያገልግል እንጂ ሁኔታን ወይም ፍላጎትን ቃል የሚገልጽ ቃል አይደለም፡፡ ሁኔታን ወይም ፍላጎትን የሚገልጸው ቃል 'iina የሚለው ቃል ነው፡፡
ስህተት 2
በሱራ 4፡162 "Laakinir-Raasi-khuuna fil-'ilmi minhum wal-Mu'-minuuna yu'-minuuna bi-maaa 'unzila 'ilayka wa maaa 'unzila min-qablika wal-muqiimiin as-Salaata wal mu'-tuunaz-Zakaata wal-Mu'-mi-nuuna billaahi wal-Yawmil-'Aakhir: 'ulaaa 'ika sanu'-tii-him 'ajran 'aziimaa." በዚህ የቁርዓን አያ Muqiimiin የሚለው ቃል በስሀተት የገባ ቃል ነው ምክንያቱም ቃሉ የገባው እንደጠቋሚ ወይም አመልካች ሆኖ ነው፡፡ ነገርግን በስዋሰው ህግ መሰረት መግባት የነበረበት muqiimuun የሚለው ቃል ነው፡፡
ስህተት 3
በሱራ 20፡63 "Qaaluuu inna haazaani la-saahiraani ..." በዚህ የቁርዓን አያ haazaani የሚለው ቃል በስህተት የገባ ቃል ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ ቃል በፊት የገባው inna የሚለው ቃል የስም ሀረግ ያለው አረፍተ-ነገርን ወደ አመልካች አረፍተ ነገር ይቀየረዋል፡፡ ስለዚህ መግባት የነበረበት ትክክለኛ ቃል haazayn ነበር፡፡
ስህተት 4
ሱራ 2፡177 "Laysal-birra 'an-tuwalluu wujuuhakum qibalal-Mashriqi wal-Maghrib wa laakinnal-birra man 'aamana billaahi wal-Yawmil-'Akhiri wal-malaaa-'ikati wal-Kitaabi wan-nabiyyiin: wa 'aatal-maala 'alaa hubbihii zawilqurbaa wal-yataamaa wal-masaakiina wabnas-sabiili was-saaa-'iliina wa fir-riqaab: wa'aqaamas-Salaata wa 'aataz-Zakaata; wal-muufuuna bi'ahdihim 'izaa 'aahaduu was-Saabiriina fil-ba'-saaa'i wazzarraaa-'i ..." ከላይ በምናየው የቁርዓን አያ አምስት የሰዋሰው ስህተቶችን እናገኛለን፡፡ በመጀመሪያው አረፍተ-ነገር tuwalluu የሚለው ቃል የአሁን ጊዜ ድርጊትን የሚያመለክት ቃል ሲሆን ሌሎች አረፍተ-ነገሮች የሚገኙ 4 ቃሎች (ግሶች) ያለፈ ድርጊትን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ 'aaman ወደ tu'minuu;
'aata ወደ tu'tuu;
'aqaama ወደ tuqimuu;
'aata ወደ tu'tuu የሚሉት ቃላት (ግሶች) መቀየር ነበረባቸው፡፡
ስህተት 5
ሱራ 3፡59 "Inna massala 'Isaa 'indal-laahi ka-masali 'Adam; khalaqahuu min-turaabin-sum-ma qaala lahuu kun fa-yakuun." በዚህ የቁርዓን አያ yakuun የሚለው ቃል የአሁን ድርጊትን የሚያመለክት ቃል (ግስ) ሲሆን ታሪኩ ያለፈ ጊዜን የሚያመለክት በመሆኑ በትክክለኛ መግባት የነበረበት ቃል kana የሚለው ቃል (ግስ) ነበር፡፡
ስህተት 6
ሱራ 21፡3 "Laahiyatan - quluubuhum. Wa 'asarrun-najwallaziin zalamuu..." በዚህ የቁርዓን አያ 'asarrun የሚለው ቃል መምጣት የነበረበት ድርጊት ፈጻሚው (subject) 3ኛ ብዙ ቁጥር መደብ (እነርሱ) ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የዚህ አርፍተ-ነገር ድርጊት ፈጻሚው (subject) በ3ኛ ነጠላ ቁጥር መደብ ለወንድ ጾታ (እሱ) በመሆኑ መምጣት የነበረበት ቃል 'asarra የሚለው ቃል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ቃል በሌሎች የቁርዓን አያዎች በትክክል የስዋሰው አገባብ ተጽፏል፡፡ በሱራ 3፡52፣ 10፡2፣ 16፡27፣ 16፡35፣ 3፡42፣ 49፡14 መመልከት ይቻላል፡፡
ስህተት 7
ሱራ 22፡19 "haazaani Khismani 'ikhtasamuu fi rabbihim ..." በአማርኛ ቋንቋ የድርጊት ፈጻሚውን (subject) ብዛት ተከትሎ የግሱ (verb) ቅርጽ ይቀየራል፡፡ በአረብኛ ቋንቋ አንዲሁ ድርጊት ፈጻሚው (subject) ነጠላ ሲሆን፣ ሀለት ሲሆኑ እንዲሁም ሶስት ሲሆኑ የግሱ ቅርጽ ይቀየራል፡፡ ስለሆነም በዚህ የቀርዓን አያ የድርጊት ፈጻሚዎቹ (subject) ሁለት ናቸው፡፡ ስለዚህ መግባት የነበረበት ግስ (verb) 'ikhtasamuu ሳይሆን 'ikhtasamaa ነበር፡፡
ስህተት 8
ሱራ 49፡9 "wa 'in-taaa-'ifataani mi-nal-Mu'-miniinaq-tatalu fa-'aslihuu baynahumaa." የዚህም ቁርዓን አያ ስህተት አንደቀድሞው ተመሳሳይ ነው፡፡ እዚህ የቁርዓን አያ ላይ የሚታዩት ድርጊት ፈጻሚዎች (subject) ሁለት ናቸው፡፡ ስለዚህ መምጣት የነበረበት ግስ (verb) 'eq-tatalu ሳይሆን 'eqtatalata ነበር፡፡
ስህተት 9
ሱራ 63፡10 "... Rabbi law laaa 'akhartaniii 'ilaaa 'ajalin-qariibin-fa-'assaddaqa wa 'akum-minas-salihiin." በዚህ የቁራዓን አያ 'akun የሚለው ቃል በስህት የተዛመደ ቃል ነው፡፡ መሆን የነበረበት ቃል 'akuuna ነበር፡፡
ስህተት 10
ሱራ 9፡15 "was-samaaa-'i wa maa ba-naahaa." በዚህ የቁርዓን አያ ma የሚለው ቃል ወካይ ቃል ነው፡፡ ቃሉ የሚወክለው ነገሮችን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ አያ ድርጊት ፈጻሚው (subject) አላህ ነው፡፡ ስለዚህ ወክሎ መግባት ያለበት ቃል ma ሳይሆን man ነበር፡፡
ስህተት 11
ሱራ 41፡11 "... faqal laha wa lel-Arad 'iteya taw'aan aw karha qalata atayna ta'e'een." በአረብኛ ቋንቋ ምድርና ሰማይ በሴት ጾታ የሚጠሩ ስሞች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ የቁርዓን አያ ለሁለት በሴት ጾታ ለሚጠሩ ስሞች የምንጠቀመው ቃል (ግስ) ta'e'een ሳይሆን ta'e'atain ነበር፡፡ ta'e'een የሚለውን ቃል (ግስ) የምንጠቀመው ለብዙ ቁጥር በወንዶች ለሚጠሩ ስሞች ነው፡፡
ስህተት 12
ሱራ 7፡160 "wa qata'nahom 'ethnata 'ashrata asbatan." በዚህ የቁርዓን አያ መግባት ያለበት ቃል asbatan ሳይሆን sebtan ነበር፡፡ ምክንያቱም asbatan የሚለው ቃል ከብዙ ቁጥር ስሞች ቀጥሎ የሚመጣ ቃል (ግስ) ነው፡፡ ምንአልባት በሌሎች ቋንቋዎች ህግ ቢሆን ይሄ ቃል አገባቡ ትክክል ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን በዚህ የቁርዓን አያ የተጠቀሱት ስሞች 12 ናቸው፡፡ በአረብኛ ቋንቋ ደግሞ ስሞች ከ10 በላይ ከሆኑ የምንጠቀመው ቃል ለነጠላ ቁጥር የምንጠቀመውን ቃል ነው፡፡ ይህ ህግ በሱራ 7፡142፣ 2፡60 ፣ 5፡12 ፣ 9፡36 ፣ 12፡4 ተፈጻሚ ሲሆን እናያዋለን፡፡
ስህተት 13
ሱራ 7፡56 "... inna rahmata Allahi qaribun min al-mohseneen." ይህ የቁርዐን አያ ያለው አረፍተ-ነገር ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ በዚህ ሀረግ ደግሞ ተሳቢው ከድርጊት ፈጻሚው (subject) መዛመድ ይኖርበታል፡፡ የሀረጉ ድርጊት ፈጻሚ (subject) ደግሞ rahmata ነው፡፡ ቃሉ ጾታን የሚገልጽ ስማዊ ሀረግ ሆኖ ያገልግላል፡፡ qaribun የሚለው ቃል rahmata Allahi ለሚለው ቃል ተሳቢ ነው፡፡ ስለዚህ አስቀድመን አንደጠቀስነው ሁለቱ ቃላት ማለትም ተሳቢው (qaribun) ድርጊት ፈጻሚው (rahmata) መዛመድ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ የቁርዓን አያ እነዚህ ሁለት ቃላት አልተዛመዱም፡፡ ስለሆንም rahmata Allahi የሚለው ቃል የሴት ጾታን የሚወክል ቃል በመሆኑ ተሳቢው መሆን የነበረበት qaribun ሳይሆን qaribah ነበር፡፡ ይህ ህግ በሱራ 9፡40 ተፈጻሚ ሲሆን እናየዋለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የሙስሊም ምሁሩ ኢብን አል ኪታብ በአል ፉርቃን መጽሐፉ የመሀመድ ሚስት የነበረቸው አይሻ በቁርዓን ጽሁፍ ስህተት 3 ብቻ የሰዋሰው ስህተተቶች መኖራቸውን ማመኗን ጽፏል፡፡ ከዚህ በመነሳት ሁለት ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል፡፡ 1ኛ. ሙስሊሞች እንደሚሉት አሁን በእጃቸው ያለው ቀርዓን መሀመድ በህይወት በነበረበት ጊዜ ከነበረው ጽሁፍ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ከሆነ አሁን ያየናቸው የሰዋሰው ስህተቶች (Grammatical Errors) የተሰሩት ከፈጣሪ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቁርዓን ከነዚህ ስህተቶቹ ከሰማይ ወረደ ካልን የፈጣሪ ቃል አይደለም ማለት ነው፡፡ 2ኛ. ቁርዓን ከነዚህ የስዋሰው ስህተቶቹ ጋር አልወረደም የሚል መከራከሪያ ካቀረብን ደግሞ አሁን ያለው ቁርዓን በመሀመድ ጊዜ ከነበረው ቁርዓን ጋር ተመሳሳይ አይደለም ማለት ነው፡፡ ተመሳሳይ ካልሆነ ደግሞ ቁርዓን ልክ እንደሌሎቹ መጽሐፍት የተበረዘ መጽሐፍ ነው ማለት ነው፡፡ ሙስሊም ወንድሞቻችን ከየትኛው ወገን ናችሁ? ስለዚህ ሰባኪዎቻችሁና መሪዎቻችሁ የሚሏችሁን አትስሙ፡፡ እውነታውን ማወቅ አለባችሁ፡፡ እግዚአብሄር ይርዳችሁ፡፡
No comments:
Post a Comment